\v 14 ከልባቸው ወደ እኔ አይጮኹም፥ ነገር ግን በአልጋዎቻችው ላይ ያለቅሳሉ። እህልና አዲስ ወይን ጠጅ ለማግኘት ራሳቸውን ለይተዋል፥ ከእኔም ዘወር ብለዋል። \v 15 እኔ ባሠለጠናቸውም፥ ክንዶቻችውንም ባበረታ፤ እነርሱ ግን ክፉ ነገርን አሴሩብኝ።