\v 12 ጽድቅን ለራሳችሁ ዝሩ፥ የኪዳኑን ታማኝንት ፍሬም እጨዱ። እስኪመጣ፥ ጽድቅንም እስኪያዝንብባችሁ ድረስ እግዚአብሔርን የምትፈልጉበት ጊዜ ነውና፤ ያልታረሰ መሬታችሁን አለስልሱ። \v 13 ክፋትን አረሳችሁ፥ግፍንም አጨዳችሁ። በስልታችሁና በወታደሮቻችሁ ብዛት ታምናችኋልና፥ የመታለልን ፍሬ በላችሁ።