am_hos_text_ulb/01/06.txt

1 line
621 B
Plaintext

\v 6 ጎሜር እንደገና ጸነሰች፥ ሴት ልጅም ወለደች። በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ሆሴዕን እንዲህ አለው፦ «ቅንጣት ታህል ይቅር እላቸው ዘንድ ከእንግዲህ ወዲያ የእስራኤልን ቤት አልምርምና ስሟን ሎሩሃማ ብለህ ጥራት። \v 7 ነገር ግን የይሁዳን ቤት እምራለሁ፥ እኔም እግዚአብሔር አምላካችው በራሴ አድናቸዋለሁ እንጂ በቀስት፥ በሰይፍ፥ በጦርነት፥ በፈረሶች ወይም በፈረሰኞች አላድናቸውም።»