\v 4 ነገር ግን ከግብጽ ምድር ያወጣሁህ አምላክህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ። ከእኔ በቀር አምላክ አታውቅም፥ ከእኔም በቀር ሌላ አዳኝ አታውቅም። \v 5 በምድረ በዳ፥ በታላቅም የድርቀት ምድር አውቅሁህ። \v 6 መሰማሪያ ባገኘህ ጊዜ ጠገብህ፥ በጠገብህም ጊዜ ልብህ ታበየ፤ከዚህም የተነሳ ረሳኽኝ።