\c 12 \v 1 ኤፍሬም ነፋስ ይመገባል፥ የምሥራቅንም ነፋስ ይከተላል። ሐሰትንና ዓመፅን ያለማቋረጥ ያበዛል። ከአሦር ጋር ኪዳን ያደርጋሉ፥ የወይራ ዘይትም ወደ ግብጽ ይወስዳሉ። \v 2 እግዚአብሔር ከይሁዳ ጋር ሙግት አለው፥ ያዕቆብንም ስላደረገው ይቀጣዋል፥ እንደ ሥራውም ይከፍለዋል።