\c 11 \v 1 እስራኤል ወጣት በነበረበት ጊዜ ወደድኩት፥ ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት። \v 2 አብዝቶ በተጠሩ መጠን፥ አብዝተው ራቁ። ለበአል አማልክት ሠው፥ ለጣዖታትም አጠኑ።