am_hos_text_ulb/10/05.txt

1 line
540 B
Plaintext

\v 5 የሰማሪያ ነዋሪዎች ከቤትአዌን ጥጃዎች የተነሳ ይፈራሉ። በእነርሱና በውብታቸው ደስ ይሰኙ የነበሩ እነዚያ ጣዖት አምላኪ ካህናት እንደሚያልቅሱላቸው፣ ሕዝቡም ያለቅሱላቸዋል፤ ከእንግዲህ ወዲያ በዚያ የሉምና። \v 6 ለታላቁ ንጉሥ እጅ መንሻ ወደ አሦር ይወሰዳሉ። ኤፍሬም ይዋረዳል፥ እስራኤልም የጣዖታትን ምክር በመከተሉ ያፍራል።