am_hos_text_ulb/09/03.txt

1 line
565 B
Plaintext

\v 3 በእግዚአብሔር ምድር ላይ አይኖሩም፤ ኤፍሬም ወደ ግብጽ ይመለሳል፥ ደግሞም አንድ ቀን በአሦር የረከሰ ምግብ ይበላሉ። \v 4 ለእግዚአብሔር የወይን ጠጅ ቁርባን አያፈሱም፤ ደስም አያሰኙትም። መስዋዕታቸው እንደ ሐዘንተኞች ምግብ ይሆንባቸዋል፦ የሚበሉት ሁሉ ይረክሳሉ። ምግባቸው ለእነርሱ ብቻ የሚሆን ነውና ወደ እግዚአብሔር ቤት ሊመጣ አይችልም።