\v 5 የእስራኤል ትዕቢት ይመሰክርባታል፤ ስለዚህ እስራኤልና ኤፍሬም በበደላቸው ይሰናከላሉ፤ ይሁዳም ከእነርሱ ጋር ትሰናከላለች። \v 6 በጎቻቸውንና ከብቶቸውን ይዘው እግዚአብሔርን ፍልጋ ይሄዳሉ፥ ነገር ግን ከእነርሱ ተለይቶ ተመልሷልና አያገኙትም። \v 7 ዲቃሎች ልጆችን ወልደዋልና ለእግዚአብሔር ታማኞች አልሆኑም። አሁንም የወር መባቻ በዓላቱ እነርሱን ከእርሻቸው ጋር ይበሉአቸዋል።