am_hos_text_ulb/04/13.txt

1 line
806 B
Plaintext

\v 13 በተራሮች ጫፍ ላይ ይሠዋሉ፥ ጥላው መልካም ነውና ከባሉጥ፥ ከኮምቦልና ከአሆማ ዛፍ በታች በኮረብቶች ላይ ያጥናሉ። ስለዚህ ሴቶች ልጆቻችሁ የዝሙት ርኩሰት ይፈጽማሉ፥ የልጆቻችሁ ሚስቶች ያመነዝራሉ። \v 14 ሴቶች ልጆቻችሁ የዝሙት ርኩሰትን በወደዱ ጊዜ፥ ወይም የልጆቻችሁ ሚስቶች ባመነዘሩ ጊዜ አልቀጣቸውም። ምክንያቱም ወንዶቹ ራሳቸውን ለሴተኛ አዳሪዎች ሰጥተዋልና፥ እንዲሁም ከቤተ ጣዖት ሴተኛ አዳሪዎች ጋር ርኩሰትን ለመፈጸም መሥዋዕት ይሰዋሉና። ስለዚህ ይህ የማያስተውል ሕዝብ ይጠፋል።