\v 14 ስለዚህ አመልሳታለሁ፥ ወደ ምድረ በዳ እወስዳታለሁ፥ በፍቅርም አነጋግራታለሁ። \v 15 የወይን ተክሏን፥ የተስፋ በርም እንዲሆናት የአኮርን ሸለቆ መልሼ እሰጣታለሁ። በዚያም በወጣትነቷ ቀናት፥ ከግብጽ ምድር በወጣችባቸው ቀናት እንዳደረገችው ትመልስልኛለች።