\v 6 ስለዚህ መንገድዋን በእሾህ ለመዝጋት አጥር እሠራለሁ። መንገድዋንም እንዳታግኝ ቅጥር እገነባባታለሁ። \v 7 ውሽሞችዋን ትከታተላቸዋለች ነገር ግን አትደርስባቸውም፤ትፈልጋቸዋለች ነገር ግን አታገኛቸውም። ከዚያም በኋላ ፦«አሁን ካለሁበት የበፊቱ ይሻላልና ወደ መጀመሪያው ባሌ እመለሳለሁ» ትላለች።