Thu Jul 13 2017 15:57:41 GMT+0300 (Jordan Daylight Time)
This commit is contained in:
parent
cca68533f6
commit
2fde53b199
|
@ -0,0 +1 @@
|
|||
\v 2 \v 3 እርሷ ሚስቴ አይደለችምና እኔም ባሏ አይደለሁምና ከእናታችሁ ጋር ተምዋግቱ፥ ተምዋገቱ። ሴተኛ አዳሪነቷን ከፊቷ፥ምንዝርናዋንም ከጡቶቿ መካከል ታስወግድ። አለበለዚያ እርቃንዋን እስክትቀር እገፋታልሁ፥እንደ ተወለደችበትም ቀን እርቃንዋን እገልጣለሁ። እንደ ምድረ በዳ እንደ ደረቅም ምድር አደርጋታለሁ፥ተጠምታ እንድትሞት አደርጋለሁ።
|
|
@ -0,0 +1 @@
|
|||
\v 4 \v 5 የሴተኛ አዳሪነት ልጆች ናቸውና ለልጆቿ ቅንጣት ምሕረት የለኝም። ምክንያቱም እናታቸው ሴተኛ አዳሪ ናትና፥ የጸንሰቻቸውም በአሳፋሪ ተግባር ነውና። እርሷም ፦«እንጀራዬንና ውኃዬን፥ሱፌንና ሐሬን፥ዘይቴንና መጠጤን ይሰጡኛልና ከውሽሞቼ ኋላ እሄዳለሁ» አለች።
|
|
@ -0,0 +1 @@
|
|||
\v 6 \v 7 ስለዚህ መንገድዋን በእሾህ ለመዝጋት አጥር እሠራለሁ። መንገድዋንም እንዳታግኝ ቅጥር እገነባባታለሁ። ውሽሞችዋን ትከታተላቸዋለች ነገር ግን አትደርስባቸውም፤ትፈልጋቸዋለች ነገር ግን አታገኛቸውም። ከዚያም በኋላ ፦«አሁን ካለሁበት የበፊቱ ይሻላልና ወደ መጀመሪያው ባሌ እመለሳለሁ» ትላለች።
|
|
@ -0,0 +1 @@
|
|||
\v 8 \v 9 እህሉን፥አዲሱን ወይን ጠጅና ዘይቱን የሰጠኋት፣ በአልን ያገለገሉበትን ብርና ወርቅ ያበዛሁላት እኔ እንደ ሆንኩ አላወቀችም። ስለዚህ እህሏን በመከር ጊዜ፥ አዲሱንም የወይን ጠጄን በወቅቱ መልሼ እወስዳለሁ። እርቃኗንም የምትሸፍንበትን ሱፌንና ሐሬን መልሼ እወስዳለሁ።
|
|
@ -0,0 +1,2 @@
|
|||
\v 10 \v 11 ከዚያም ውሽሞችዋ እያዩ እርቃንዋን እስክትቀር ድረስ እገፋታለሁ፥ ከእጄም ማንም አያስጥላትም።ሁሉንም ክብረ በዓላቷን፦ የደስ
|
||||
ታ በዓላቷን፥የአዲስ ጨረቃ ክብረ በዓላቷን፥ሰንበታቷንና ዓመታዊ በዓላቷን አስቀራለሁ።
|
|
@ -0,0 +1 @@
|
|||
\v 12 \v 13 «ውሽሞቼ የሰጡኝ ክፍያዎቼ ናቸው» የምትላቸውን ወይንዋንና የበለስ ዛፎችዋን አጠፋለሁ። ጫካ አደርጋቸዋለሁ፥ የዱር አራዊትም ይበሉዋቸዋል። ለበአል አማልክት ዕጣን ስላጠነችባቸው፥ በቀለበቶችዋና በጌጣ ጌጦቿ ራስዋን ስላስዋበችባቸው እና እኔን ረስታ ከውሽሞቿ ኋላ ስልሄደችባችው የደስታ በዓላት እቀጣታለሁ።» ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።
|
|
@ -0,0 +1 @@
|
|||
\v 14 \v 15 ስለዚህ አመልሳታለሁ፥ወደ ምድረ በዳ እወስዳታለሁ፥በፍቅርም አነጋግራታለሁ። የወይን ተክሏን፥የተስፋ በርም እንዲሆናት የአኮርን ሸለቆ መልሼ እሰጣታለሁ። በዚያም በወጣትነቷ ቀናት፥ ከግብጽ ምድር በወጣችባቸው ቀናት እንዳደረገችው ትመልስልኛለች።
|
Loading…
Reference in New Issue