am_hos_text_udb/05/05.txt

3 lines
1.1 KiB
Plaintext

\v 5 ስራኤል ታብያለች፤ ከዚህም የተነሣ ምን ያህል በደለኛ እንደ ሆነች ሌሎች ያውቃሉ፤ የእስራኤል ሕዝብ የፈጸሟቸው ኃጢአቶች በእግዚአብሔር ዘንድ እምነተ ቢሶች አድርገዋቸዋል፤ ይሁዳም እንደዚሁ እምነተ ቢስ እየሆነ ነው፡፡
\v 6 ምሕረት እንዲያደርግላቸው እግዚአብሔርን እንደሚያግባቡ ተስፋ እያደረጉ ነው፤ ከመንጎቻቸውና ከከብቶቻቸው በጎችንና ከብቶችን ለመሠዋት ይመጣሉ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር እነርሱን መርዳት ስላቆመና ስለ ተዋቸው ለእነርሱ ምንም ምሕረት እንደማያደርግላቸው ይረዳሉ፡፡
\v 7 ለእግዚአብሔር የገቧቸውን ቃል ኪዳኖች አልጠበቁም፤ ከእንግዶች ሴቶችም ልጆችን ወልደዋል፤ ስለዚህ በዐዲስ ጨረቃ በዓላት ወቅት ካለሟቸው የዕርሻ ስፍራዎች ጋር ይጠፋሉ፡፡››