am_heb_text_ulb/12/01.txt

1 line
823 B
Plaintext

\c 12 \v 1 \v 2 \v 3 1 እንደነዚህ ያሉ እጅግ ብዙ ምስክሮች ስላሉን፣ የሚከብደንን ነገር ሁሉና በቀላሉ የሚጠላልፈንን ኃጢአት አሽቀንጥረን እንጣል። ከፊታችን ያለውንም ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ። 2 በእምነታችን ጀማሪና ፍጹም አድራጊ ኢየሱስ ላይ ዓይኖቻችን እንትከል። እርሱ ከፊቱ ስላለው ደስታ መስቀሉንና መስቀሉ የሚያስከትለውን ውርደት ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል። 3 እንዳትደክሙ ወይም ልባችሁ እንዳይዝል፣ ከኃጢአተኞች የተሰነዘረበትን እንዲህ ያለውን የጥላቻ ንግግር የታገሠውን እርሱን አስቡ።