am_heb_text_ulb/11/32.txt

1 line
640 B
Plaintext

\v 32 \v 33 \v 34 32-33 እንግዲህ ከዚህ የበለጠ ምን ልበል? በእምነት መንግሥታትን ድል ስላደረጉት፣ ፍትህን ስላስከበሩትና የተስፋ ቃሎችን ስለተቀበሉት ስለነጌደዎን፣ ባርቅ፣ ሳምሶን፣ ዮፍታሄ፣ ዳዊት፣ ሳሙኤልና ነቢያት እንዳልናገር ጊዜ ያጥረኛል። 34 እነርሱ የአንበሶችን አፍ ዘጉ፣ የእሳትን ኃይል አጠፉ፣ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፣ ከበሽታ ተፈወሱ፣ በጦርነት ኃያላን ሆኑ፥ የባዕድን ሠራዊት አባረሩ።