am_heb_text_ulb/11/23.txt

1 line
794 B
Plaintext

\v 23 \v 24 \v 25 \v 26 23 ሙሴ ሲወለድ ወላጆቹ መልከ መልካም ሕፃን መሆኑን አይተው የንጉሡን ትእዛዝ ሳይፈሩ ለሦስት ወራት የደበቁት በእምነት ነበር። 24 ሙሴም ካደገ በኋላ የፈርዖን የልጅ ልጅ፣ እንዳይባል እምቢ ያለው በእምነት ነበር። 25 ለአጭር ጊዜ በኃጢአት ደስ ከመሰኘት ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራን መካፈልን መረጠ። 26 ዓይኖቹ ወደፊት የሚቀበለውን ዋጋ አተኩረው ስለተመለከቱ፣ በግብጽ ከሚገኝ ሀብት ይልቅ ክርስቶስን መከተል የሚያስከትልበትን ውርደት የላቀ ብልጽግና አድርጎ አሰበ።