am_heb_text_ulb/11/08.txt

1 line
610 B
Plaintext

\v 8 \v 9 \v 10 8 አብርሃም በተጠራ ጊዜ ርስትን ወደሚቀበልበት ቦታ ታዞ የሄደው በእምነት ነበር። የወጣው ወዴት እንደሚሄድ ሳያውቅ ነበር። 9 በተስፋው ምድር እንደ ባዕድ የኖረውም በእምነት ነበር። ያን ተስፋ ከእርሱ አብረው ከሚወርሱት እንደ ይስሐቅና እንደ ያዕቆብ በድንኳን ውስጥ ኖረ። 10 ይሄውም እግዚአብሔር መሠረት ያላትን፣ ያቀዳትንና ያነጻትን ከተማ ይጠባበቅ ስለነበር ነው።