am_heb_text_ulb/10/01.txt

1 line
976 B
Plaintext

\c 10 \v 1 \v 2 \v 3 \v 4 1 ሕጉ ሊመጡ ላሉ መልካም ነገሮች ጥላ ብቻ እንጂ እውነተኛው አካል አይደለም። ሕጉ ካህናት ያለማቋረጥ በየዓመቱ በሚያቀርቧቸው በነዚያው መሥዋዕቶች ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡትን ከቶ ፍጹም ሊያደርጋቸው አይችልም። 2 ቢችል ኖሮ እነዚያ መሥዋዕቶች መቅረባቸው ይቀር አልነበረምን? እንደዚያ ቢሆን ኖሮ የሚያመልኩት አንድ ጊዜ ከኃጢአታቸው ከነጹ በኋላ ስለ ኃጢአታቸው የሚያስታውሱት ነገር ምንም አይኖርም ነበር። 3 ነገር ግን በእነዚያ መሥዋዕቶች ውስጥ በየዓመቱ የተፈጸሙትን ኃጢአቶች የሚያስታውስ ነገር አለ። ለዚህ ምክንያቱ የኮርማዎችና የበጎች ደም ኃጢአትን ማስወገድ ባለመቻሉ ነው።