am_heb_text_ulb/06/04.txt

1 line
606 B
Plaintext

\v 4 ይህንን የምናደርገው አንድ ጊዜ ብርሃን በርቶላቸው ሰማያዊውን ስጦታ የተቀበሉትን፣ከመንፈስ ቅዱስ ተሳታፊዎች የነበሩትን፣ \v 5 መልካሙን የእግዚአብሔር ቃልና በመጪው ዘመን ሊመጣ ያለውን ኃይል ከቀመሱ በኃላ \v 6 የካዱትን በንስሐ እንዲታደሱ ማድረግ የማይቻል በመሆኑ ነው። እነዚህ ለሕዝብ መሳለቂያ ይሆን ዘንድ ራሱን የእግዚአብሔርን ልጅ ራሳቸው እንደገና ይሰቅሉታል።