am_heb_text_ulb/01/01.txt

1 line
648 B
Plaintext

\c 1 \v 1 \v 2 \v 3 1 ከረጅም ጊዜ በፊት በተለያዩ ዘመናትና በተለያዩ መንገዶች እግዚአብሔር በነቢያት በኩል ለአባቶቻችን ተናግሮ ነበር። 2 አሁን ግን የሁሉም ነገር ወራሽ ባደረገው፣ ዓለምንም በፈጠረበት በልጁ ተናገረን። 3 ልጁ የክብሩ ነጸብራቅ ነው፤ እርሱ በባሕርዩ ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም አንድ ነው፤ በሥልጣን ቃል ሁሉን ደግፎ ይዞአል። የሰዎችንም ኃጢአት ካነዳ በኃላ በሰማይ በግርማው ቀኝ ተቀምጧል።