am_hag_text_ulb/02/10.txt

1 line
689 B
Plaintext

\v 10 ዳርዮስ በነገሠ ሁለተኛው ዓመት፣ በዘጠነኛው ወር ሃያ አራተኛ ቀን የያህዌ ቃል በነቢዩ በሐጌ በኩል መጣ፤ እንዲህም አለ፣ \v 11 “የሠራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ ሕጉ ምን እንደሚል ካህናቱን ጠይቁ፤ \v 12 አንድ ሰው ለያህዌ የተቀደሰውን ሥጋ በልብሱ እጥፋት ቢይዝ፣ በልብሱ እጥፋት እንጀራ ወይም ወጥ፣ የወይን ጠጅ ወይም ዘይት ወይ ሌላ ምግብ ቢነካ፣ ያ ምግብ ይቀደሳልን?” ካህናቱም፣ “የለም፣ አይቀደስም” በማለት መለሱ።