am_hab_text_ulb/02/18.txt

11 lines
697 B
Plaintext
Raw Permalink Blame History

This file contains ambiguous Unicode characters

This file contains Unicode characters that might be confused with other characters. If you think that this is intentional, you can safely ignore this warning. Use the Escape button to reveal them.

\v 18 ታዲያ፣ የቀረጽኸው ምስል ምን ይጠቅምሃል?
ምስሉን የቀረጸው፣ ከቀለጠ ብረት ጣዖት የሠራ ሰው
የሐሰት መምህር ነው፤
እነዚያን የማይናገሩ አማልክት ሲሠራ
በገዛ እጅ ሥራው ተማምኖአልና፡፡
\v 19 ዕንጨቱን ንቃ! ሕይወት የሌለውንም ድንጋይ ተነሣ ለሚል ወዮለት
ለመሆኑ፣ እነዚህ ነገሮች ማስተማር ይችላሉን?
በወርቅና በብር ተለብጦአል፤
እስትንፋስ ግን የለውም፡፡
\v 20 ያህዌ ግን በተቀደሰ መቅደሱ አለ፤
ምድር ሁሉ በፊቱ ጸጥ ትበል!