Thu Jun 21 2018 09:23:13 GMT+0300 (E. Africa Standard Time)

This commit is contained in:
kaleab 2018-06-21 09:23:15 +03:00
parent c6aef7d90a
commit 5a0f584b32
259 changed files with 268 additions and 0 deletions

1
11/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\c 11 \v 1 በዚያ ዘመን መላው ዓለም የሚናገረውና የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር። \v 2 ወደ ምሥራቅ ሲጓዙ፣ በሰናዖር አንድ ሜዳማ ቦታ አግኝተው በዚያ ሰፈሩ።

1
11/03.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 3 እርስ በርሳቸውም፣ “ኑ፣ ጡብ እንሥራና እስከበቃው ድረስ በእሳት እንተኩሰው” ተባባሉ። በድንጋይ ፈንታ ጡብ ተጠቀሙ፤ ጡቡን እርስ በርስ ለማያያዝም ቅጥራን ተጠቀሙ። \v 4 ከዚያም፣ “ለስማችን መጠሪያ እንዲሆን ጫፉ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ። ያንን ካላደረግን በምድር ሁሉ ፊት መበታተናችን ነው” አሉ።

1
11/05.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 5 የአዳም ልጆች የሠሩትን ለማየት ያህዌ ወደ ከተማውና ወደ ግንቡ ወረደ። \v 6 ያህዌም፣ “አንድ ቋንቋ የሚናገሩ አንድ ሕዝብ በመሆናቸው ይህን ማድረግ ችለዋል! ከእንግዲህ ማድረግ የፈለጉትን ለማድረግ ምንም የሚያቅታቸው አይኖርም። \v 7 ኑ እንውረድ፤ አርስ በርስ እንዳይግባቡም ቋንቋቸውን እንደበላልቀው” አለ።

1
11/08.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 8 ስለዚህ ያህዌ ከዚያ ቦታ ወደ መላው ዓለም በታተናቸው፣ እነርሱም ከተማዋን መሥራት አቋረጡ። \v 9 በዚያ የዓለምን ቋንቋ ስለ ደበላለቀ የከተማዋ ስም ባቤል ተባለ። ከዚያም ያህዌ በመላው ዓለም በተናቸው።

1
11/10.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 10 የሴም ትውልድ ይህ ነው። የጥፋት ውሃ ከመጣ ሁለት ዓመት በኋላ ሴም መቶ ዓመት ሲሆነው አርፋድሰድን ወለደ። \v 11 አርፋድሰድን ከወለደ በኋላ ሴም አምስት መቶ ዓመት ኖረ። ሌሎች ወንዶች እና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።

1
11/12.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 12 አርፋክሰድ በሰለሣ አምስት ዓመቱ ሰላን ወለደ፤ \v 13 ሰላን ከወለደ በኋላ አርፋክሰድ አራት መቶ ሦስት ዓመት ኖረ፤ እርሱም ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።

1
11/14.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 14 ሳላ ሰላሣ ዓመት ሲሆነው ዔቦርን ወለደ፤ \v 15 ዔቦርን ከወለደ በኋላ ሳላ አራት መቶ ሦስት ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።

1
11/16.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 16 ዔቦር አራት ዓመት ሲሆነው ፋሌቅን ወለደ፤ \v 17 ፋሌቅን ከወለደ በኋላ ዔቦር አራት መቶ ሰላሣ ዓመት ኖረ፤ እርሱም እንዲሁ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።

1
11/18.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 18 ፋሌቅ ሰለሣ ዓመት ሲሆነው፣ ራግውን ወለደ፤ \v 19 ራግውን ከወለደ በኋላ ፋሌቅ ሁለት መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፤ እርሱም እንዲሁ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።

1
11/20.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 20 ራግው ሰለሣ ሁለት ዓመት ሲሆነው፣ ሴሮሕን ወለደ፤ \v 21 ሴሮሕን ከወለደ በኋላ ራግው ሁለት ሞት ሰባት ዓመት ኖረ፤ እርሱም እንዲሁ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።

1
11/22.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 22 ሴሮሕ ሰለሣ ዓመት ሲሆነው፣ ናኮርን ወለደ፤ \v 23 ናኮርን ከወለደ በኋላ ሴሮሕ ሁለት መቶ ዓመት ኖረ፤ እርሱም እንዲሁ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።

1
11/24.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 24 ናኮር ሃያ ዘጠኝ ዓመት ሲሆነው ታራን ወለደ፤ \v 25 ታራን ከወለደ በኋላ ናኮር አንድ መቶ አሥራ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፤ እርሱም እንዲሁ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ። \v 26 ታራ ሰባ ዓመት ሲሆነው አብራምን፣ ናኮርንና ሐራንን ወለደ።

1
11/27.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 27 የታራ ትውልድ ይህ ነው። ታራ፣ አብራምን፣ ናኮርንና ሐራን ወለደ። ሐራን ሎጥን ወለደ። \v 28 ሐራን አባቱ ታራ በሕይወት እያለ በተወለደበት ከተማ በከለዳውያን ዑር ሞተ።

1
11/29.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 29 አብራምና ናኮር ሁለቱም ሚስት አገቡ። የአብራም ሚስት ሦራ ስትባል፣ የናኮር ሚስት ደግሞ ሚልካ ትባል ነበር፤ ሚልካ የሐራን ልጅ ስትሆን፣ ሐራን የሚልካና የዮሳካ አባት ነበር። \v 30 ሦራ ምንም ልጅ ያልነበራት መካን ነበረች።

1
11/31.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 31 ታራ ልጁ አብራምን፣ የልጅ ልጁን ሎጥንና የአብራምን ሚስት ምራቱን ሦራን ይዞ ወደ ከነዓን ለመሄድ በከለዳውያን ምድር ከምትገኘው ዑር አብረው ወጡ። ሆኖም፣ ካራን በደረሱ ጊዜ በዚያ ተቀመጡ። \v 32 ታራ ሁለት መቶ አምስት ዓመት ኖሮ በካራን ሞተ።

1
12/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\c 12 \v 1 በዚህ ጊዜ ያህዌ አብራምን እንዲህ አለው፤ “አገርህን፣ ወገንህንና የአባትህን ቤተ ሰብ ትተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ሂድ፤ \v 2 ታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ፤ እባርክሃለሁ፤ ስምህን ገናና አደርገዋለሁ፤ ለሌሎችም በረከት አደርግሃለሁ። \v 3 የሚባርኩህን እባርካለሁ፤ የሚረግሙህንና የሚያዋርዱህን እረግማለሁ። በአንተ አማካይነት በምድር የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ይባረካሉ።”

1
12/04.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 4 ስለዚህ አብራም ያህዌ እንዳዘዘው ወጣ፤ ሎጥም አብሮት ሄደ። አብራም ከካራን ተነሥቶ ሲሄድ፣ የሰባ አምስት ዓመት ሰው ነበር። \v 5 አብራም ሚስቱ ሦራን፣ የውንድሙ ልጅ ሎጥን አስከትሎ በካራን ያፈሩትን ሀብትና የነበራቸውን አገልጋዮች ይዞ በመጓዝ፣ ከነዓን ምድር ገቡ።

1
12/06.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 6 አብራም በሞሬ ያለው ግዙፍ የወርካ ዛፍ እስካለበት እስከ ሴኬም ዘልቆ ሄደ። በዚያ ዘመን ከነሻናውያን በዚህ ምድር ይኖሩ ነበር። \v 7 ያህዌ ለአብራም ተገልጦ፣ “ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ” አለው። ስለዚህ አብራም ለተገለጠለት ለያህዌ በዚያ መሠዊያ ሠራ።

1
12/08.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 8 ከዚያ በመነሣት ከቤቴል በስተ ምሥራቅ ወዳለው ተራራማ አገር ሄደ፤ ቤቴል በስተ ምዕራብ፣ ጋይ በስተ ምዕራብ ባለችበት ቦታ ድንኳኑን ተከለ። እዚያ ለያህዌ መሠዊያ ሠራ፤ የያህዌንም ስም ጠርቶ ጸለየ። \v 9 አብራም ከዚያ ተነሥቶ ወደ ኔጌብ መጓዙን ቀጠለ።

1
12/10.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 10 በዚያ ምድር ጽኑ ራብ ስለ ነበር አብራም እዚያ ጥቂት ጊዜ ለመቆየት ወደ ግብፅ ሄደ። \v 11 ግብፅ በመግባት ላይ እያለ አብራም ሚስቱ ሦራን እንዲህ አላት፤ “መቼም አንቺ ቆንጆ ሴት መሆንሽን አውቃለሁ። \v 12 ግብፃውያን ሲያዩሽ ‘ይህች ሚስቱ ናት’ ይላሉ፤ እኔን ይገድሉኛል፤ አንቺን ግን ይተዉሻል። \v 13 ስለዚህ በአንቺ ምክንያት ለእኔ መልካም እንዲሆልኝ ሕይወቴም እንዲተርፍ እኅቱ ነኝ’ በዪ አላት።

1
12/14.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 14 አብራም ወደ ግብፅ ሲገባ፣ ሦራ ምን ያህል ቆንጆ እንደ ሆነች ግብፃውያኑ አዩ። \v 15 የፈርሾን ሹማምንት ባዩአት ጊዜ እርሷን እያደነቁ ለፈርዖን ነገሩት፤ ወደ ቤተ መንግሥትም ተወሰደች። \v 16 በእርሷ ምክንያት ፈርኦን አብራምን በክብር አስተናገደው፤ በጎች፣ በሬዎች፣ ወንድ አህዮች ወንድና ሴት ባሪያዎች፣ ሴት አህዮችና ግመሎች ሰጠው።

1
12/17.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 17 በአብራም ሚስት በሦራ ምክንያት ያህዌ ፈርዖንና ቤተ ሰቡን በታላቅ መቅሠፍት መታ። \v 18 ፈርዖን አብራምን አስጠርቶ እንዲህ አለው፤ “ለመሆኑ ምን እያደረግህብኝ ነው? ሚስትህ መሆንዋን ለምን አልነገርከኝም? \v 19 ለምን እኅቴ ናት አልከኝ? እኅቴ ናት ስላልከኝ ሚስቴ ላደርጋት ነበር። አሁንም ሚስትህ እቻት፤ ይዘሃት ሂድ” \v 20 ከዚያም ፈርዖን አብራምን በተመለከተ ለባለሟሎቹ ትእዛዝ ሰጠ፤ እነርሱም አብራምን ከሚስቱና ከንብረቱ ሁሉ ጋር አሰናበቱት።

1
12/title.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
ምዕራፍ 12

1
13/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\c 13 \v 1 ስለዚህ አብራም ሚስቱንና ያለውን ንብረት ሁሉ ይዞ ከግብፅ ወደ ኔጌብ ሄደ። ሎጥም ከእነርሱ ጋር ነበረ። \v 2 በዚህ ጊዜ አብራም በከብት፣ በብርና በወርቅ በልጽጎ ነበር።

1
13/03.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 3 ከኔጌብ ተነሥቶ እስከ ቤቴል ተጓዘ፤ ቀድሞ ድንኳን ተክሎበት ወደ ነበረው በቤቴልና በጋይ መካከል ወደ ነበረው ቦታ ደረሰ። \v 4 ይህ ቀድሞ መሠዊያ የሠራበት ቦታ ሲሆን በዚያ ያህዌን ጠራ።

1
13/05.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 5 ከአብራም ጋር ይጓዝ የነበረው ሎጥ የራሱ በጎች፣ ከብቶችና ድንኳኖች ነበሩት። \v 6 ሁለቱ አንድ ላይ ይኖሩ ስለ ነበር ስፍራው አልበቃቸውም፤ በዚህ ላይ ንብረታቸውም በጣም ብዙ ስለ ነበር አብረው መኖር አልቻሉም። \v 7 ይህም በመሆኑ በአብራምና በሎጥ እረኞች መካከል ጠብ ተፈጠረ። በዚያ ዘመን ከነኣናውያንና ፌርዛውያን በዚያው አገር ይኖሩ ነበር።

1
13/08.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 8 አብራም ሎጥን እንዲህ አልው፤ “በእኔና በአንተ፣ በእኔ እረኞችና በአንተ እረኞች መካከል ግጭት መኖር የለበትም፤ በዚህ ላይ ደግሞ ቤተ ሰብ ነን። \v 9 ይኸው እንደምታየው ምድሩ ሰፊ ነው፤ ብንለያይ ይሻላል። አንተ ግራውን ብትመርጥ፣ እኔ ወደ ቀኝ እሄዳለሁ፤ ወይም አንተ ቀኙን ብትመርጥ እኔ ወደ ግራ እሄዳለሁ።

1
13/10.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 10 ስለዚህ ሎጥ ዙሪያውን ሲመለከት እስከ ዞዓር ድረስ ያለው የዮርዳኖስ ረባዳ ሜዳ ሁሉ እንደ ያህዌ ገነት እንደ የግብፅ ምድር በጣም ለም ሆኖ አገኘው። እንዲህ የነበረው እግዚአብሔር ሰዶምና ገሞራን ከማጥፋቱ በፊት ነበር። \v 11 ሎጥ የዮርዳኖስን ረባዳ ሜዳ ሁሉ መርቶ ወደ ምሥራቅ ተጓዘ፤ በዚህ ሁኔታ ዘመዳሞቹ ተለያዩ።

1
13/12.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 12 አብራም መኖሪያውን በከነዓን ምድር አደረገ፤ ሎጥ ግን በረባዳው ሜዳ ባሉት ከተሞች መካከል ኖረ። እስከ ሰዶም ድረስ ባለው ቦታ ድንኳኖቹን ተከለ። \v 13 የሰዶም ሰዎች በጣም ዐመፀኞችና በያህዌም ፊት እጅግ ኀጢአተኞች ነበሩ።

1
13/14.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 14 ሎጥ ከእርሱ ከተለየው በኋላ ያህዌ አብራምን እንዲህ አለው፤ “ካለህበት ቦታ ወደ ሰሜን፣ ወደ ደቡብ፣ ወደ ምሥራቅና ምዕራብ ተመልከት። \v 15 ይህን የምታየውን ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘርህ ለዘላለም እሰጣለሁ።

1
13/16.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 16 ዘርህን እንደ ምድር ትቢያ አበዛዋለሁ፤ የምድር ትቢያ ሊቆጠር እንደማይቻል ሁሉ የአንተም ዘር ሊቆጠር አይችልም። \v 17 እንግዲህ ምድሪቱን ስለምስጥህ ተነሣና በርዝመትና በስፋቱ ተመላለሰባት።” \v 18 ስለዚህ አብራም ድንኳኑን ነቀለና በኬብሮን ወዳሉት የመምሬ ወርካ ዛፎች መጥቶ ኖረ፤ እዚያም ለያህዌ መሠዊያ ሠራ።

1
13/title.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
ምዕራፍ 13

1
14/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\c 14 \v 1 አምራፌል የሰናዖር ንጉሥ፣ አርዮክ የአላሳር ንጉሥ፣ ከሎደጎምር የኤላም ንጉሥ፣ ተድዓል የጎይም ንጉሥ፣ \v 2 በነበሩበት ዘመን፤ ከሰዶም ንጉሥ በላ፣ ከጎሞራ ንጉሥ ከብርሳ፣ ከአዳማ ንጉሥ ከሰነአብ፣ ከሰቦይ ንጉሥ ከሰሜበር፣ እንዲሁም ዞዓር ከተባለች ከቤላ ንጉሥ ጋር ለመዋጋት ወጡ።

1
14/03.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 3 እነዚህ የኋለኞቹ አምስት ነገሥታት የጨው ባሕር እየተባለች በምትጠራው በሲዶም ሸለቆ ተሰበሰቡ። \v 4 እነርሱም አሥራ ሁለት ዓመት ለኮሎዶጎምር ተገዙ፤ በአሥራ ሦስተኛው ዓመት ግን ዐመፁ። \v 5 በአሥራ አራተኛው ዓመት ከሎዶጎምርና ከእርሱም ጋር የነበሩት ነገሥታት መጥተው ራፋይምን፣ በአስታሮት ቃርናይምን፣ በካም ዙዚምን፣ በሴዊ ኑሚምን፣ በሸቮት ኢምንን፣ \v 6 የሖር ሰዎችንም በተራራማው አገር በሴይ በረሐማ አጠገብ እስካለው እስከ አልፋራን ድረስ ድል አደረጋቸው።

1
14/07.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 7 ከዚያም ተመልሰው ዓይንሚስፓጥ ወደሚባለው ወደ ቃዴስ መጡ፤ የአማሌዋውያንና በሐሴስ ታማር ይኖሩ የነበሩትን የአሞራውያን ግዛት በሙሉ ድል አድርገው ያዙ። \v 8 ከዚያም የሶዶም፣ የገሞራ፣ የአዳማ፣ የሰቦይ እንዲሁም ዞዓር የተባለችው የቤላ ነገሥታት ወደ ሲዶም ሸለቆ ሄደው ለጦርነት ተዘጋጁ። \v 9 እነዚህ አምስቱ በኤላም ንጉሥ በኮሎዶጎምር፣ በጎይም ንጉስ በቲድዓል፣ በሰናዖር ንጉሥ በአምራፌል፣ በአላሶር ንጉሥ በአርዮክ በእነዚህ ላይ ዘመቱባቸው።

1
14/10.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 10 በሲዲም ሸለቆ ብዙ የቅጥራን ጉድጓዶች ነበሩ፤ የሰዶምና የጎመራ ነገሥታት ሲሸሹ ከሰዎቻቸው አንዳንዶቹ በእነዚህ ጉድጓዶች ውስጥ ወደቁ። የተረፉትም ወደ ተራሮች ሸሹ። \v 11 አራቱ ነገሥታትም በሰዶምና በጎሞራ ያገኙትን ሀብትና ምግብ ሁሉ ዘርፈው ሄዱ። \v 12 በሰዶም ይኖር የነበረውን የአብርሃምን ወንድም ልጅ ሎጥንና የነበረውን ንብረት ሁሉ ይዘው ሄዱ።

1
14/13.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 13 ከዚያ ያመለጠ አንድ ሰው መጥቶ ለዕብራዊው ለአብራም ነገረው። በዚያ ጊዜ ይኖር የነበረው የአስኮና የእውናን ወንድም በነበረው በአሞራዊው መምሬ ዋርካ ዛፎች አጠገብ ነበር፤ እነዚህ ሁሉ የአብራም አጋሮች ነበር። \v 14 ጠላት ዘመዶቹን ማርኮ መውሰዱን አብራም ሲሰማ በቤቱ ተወልደው ያደጉ ሦስት መቶ አሥራ ስምንት ሰዎች ይዞ እስከ ዳን ድረስ ተከታተሏቸው።

1
14/15.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 15 አብራም ጠላቶቹን ለማጥቃት ሰራዊቱን ሌሊቱን በቡድን በቡድን ከፋፍሎ ከደማስቆ በስተ ሰሜን እስከሚገኘው እስከ ሖባ ድረስ አሳደዳቸው። \v 16 ጠላት የማረከውን በሙሉ አስጣለ፤ ዘመዱ ሎጥንና ንብረቱን፣ እንዲሁም ሴቶቹንና ሌሎች ሰዎችን አስመለሰ።

1
14/17.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 17 አብራም የኮሎዶጎምርንና ከእርሱ ጋር የነበሩ ነገሥታትን ድል አድርጎ ሲመለስ የሰዶም ንጉሥ የንጉሥ ሸለቆ ተብሎ በሚጠራው በሴዊ ሸለቆ ሊቀበለው ወጣ። \v 18 የሰሌም ንጉሥ መልከጼዴቅ እንጀራና ወይን ጠጅ ይዞ መጣ። እርሱ የልዑል አምላክ ካህን ነበር።

4
14/19.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,4 @@
\v 19 አብራምም እንዲህ በማለት ባረከው፣
“ሰማይና ምድርን የፈጠረ ልዑል እግዚአብሔር አብራምን ይባርክ።
\v 20 ጠላቶችህን በእጅህ አሳልፎ የሰጠ ልዑል እግዚአብሔር ይባረክ።”
አብራምም ይዞት ከነበረው ሁሉ አንድ አሥረኛውን ሰጠው።

1
14/21.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 21 የሰዶም ንጉሥ አብራምን፣ “ሰዎቹን ለእኔ ስጠኝ፤ ንብረቱን ግን ለራስህ አስቀር” አለው። \v 22 አብራምም ለሰዶም ንጉሥ እንዲህ አለው፤ “ከአንተ ብጣሽ ክርም ሆነ የጫማ ማሰሪያ እንኳ ቢሆን፣ \v 23 ደግሞም ‘አብራምን ባለጸጋ አደረግሁት’ እንዳትል የአንተ ከሆነ ምንም ነገር እንዳልወስድ ሰማይና ምድርን ወደ ፈጠረ አምላክ ወደ ያህዌ እጄን አንሥቻለሁ። \v 24 አብረውኝ ያሉት ሰዎች ከበሉትና የእነርሱ ድርሻ ከሆነው በቀር ምንም ነገር አልወስድም። አውናን፣ ኤስኩልና መምሬ ድርሻቸውን ይውሰዱ።”

1
14/title.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
ምዕራፍ 14

1
15/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\c 15 \v 1 ከዚህ በኋላ የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል ወደ አብራም መጣ፤ “አብራም ሆይ፣ አትፍራ፤ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ፤ ታላቅ ሽልማትህም እኔው ነን።” \v 2 አብራምም፣ “ጌታ ያህዌ ሆይ፣ እኔ ልጅ የለኝም፤ የቤት ወራሽ የሚሆነው የደማስቆው ሰው ኤሊዔዘር ነው፤ ታዲያ አንተ ለእኔ የምትሰጠኝ ምንድን ነው?” አለ። \v 3 በመቀጠልም አብራም “አንተ ልጅ እስካልሰጠኸኝ ድረስ፣ ከቤቴ አገልጋይ አንዱ ወራሼ መሆኑ አይቀርም” አለ።

1
15/04.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 4 በዚህ ጊዜ የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እርሱ መጣ፤ “ይህ ሰው ወራሽህ አይሆንም፤ ይልቁንም ወራሽህ የሚሆነው ከአብራክህ የሚከፈል የራስህ ልጅ ይሆናል።” \v 5 ከዚያም ወደ ውጭ አወጣውና እንዲህ አለው፤ “ቀና ብለህ ወደ ሰማይ ተመልከት፤ መቍጠር ከቻልህ ከዋክብቱን ቍጠር። ዘርህም እንዲሁ ይበዛል።”

1
15/06.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 6 አብራም ያህዌን አመነ፤ እርሱም ጽድቅ አድርጎ ቆጠረለት። \v 7 እንዲህም አለው፤ “ይህችን ምድር እንድትወርስ ልሰጥህ ከከለዳውያን ምድር ከዑር ያወጣሁህ እኔ ያህዌ ነኝ።” \v 8 አብራምም፣ “ጌታ ያህዌ ሆይ፣ ይህችን ምድር እንደምወርስ እንዴት አውቃለሁ?” አለ።

1
15/09.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 9 በዚህ ጊዜ፣ “እያንዳንዳቸው ሦስት ዓመት የሆናቸው አንዲት ጊደር፣ አንዲት ፍየልና አንድ በግ እንዲሁም ዋኖስና አንድ ርግብ አቅርብልኝ” አለው። \v 10 እርሱም እነዚህን ሁሉ አቀረበለት፤ ቆርጦም ሁለት ቦታ ከከፈላቸው በኋላ እያንዳንዱን ክፍል በሌላው ወገን ትይዩ አስቀመጣቸው፤ ወፎቹን ግን አልከፈላቸውም። \v 11 አሞሮች ሥጋውን ለመብላት ወረዱ፤ አብራምም አባረራቸው።

1
15/12.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 12 ፀሓይ ልትጠልቅ ስትል አብራም ከባድ እንቅልፍ ወሰደው፤ የሚያስፈራም ድቅድቅ ጨለማም መጣበት። \v 13 በዚህ ጊዜ ያህዌ አብራምን እንዲህ አለው፤ “ዘሮችህ የራሳቸው ባልሆነ ምድር ባዕድ እንደሚሆኑና እዚያ ለአራቶ መቶ ዓመት በባርነት እንደሚኖሩ በእርግጥ ዕወቅ።

1
15/14.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 14 እኔም ባሪያዎች ባደረጓቸው ሕዝብ እፈርዳለሁ፤ በኋላም ብዙ ሀብት ይዘው ይወጣሉ። \v 15 አንተ ግን በሰላም ወደ አባቶችህ ትሄዳለህ፤ ዕድሜም ጠግበህ ትቀበራለህ። \v 16 በአራተኛውም ትውልድ እንደ ገና ወደዚህ ይመጣሉ፤ ምክንያቱም የአሞራውያን ኀጢአት ጽዋው ገና አልሞላም።”

1
15/17.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 17 ፀሓይ ገብታ ከጨለመ በኋላ የምድጃ ጢስና የሚንበለበል ፋና በተቆራረጡት ሥጋዎች መካከል አለፈ። \v 18 በዚያን ቀን ያህዌ እንዲህ በማለት ከአብራም ጋር ኪዳን አደረገ፤ “ከግብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ታላቁ ወንዝ ኤፍራጥስ ድረስ ያለውን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ፤ \v 19 የምሰጣቸውም የቄናውያንን፣ የቄንፌዛውያንን፣ የቃድሞናውያንን፣ \v 20 የኬጢያውያንን፣ የፌርዛውያንን፣ የራፋይምን፣ \v 21 የአሞራውያንን፣ የከነዓናውያን፣ የጌርሳውያንንና የኢያቡሳውያን ምድር ነው።”

1
15/title.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
ምዕራፍ 15

1
16/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\c 16 \v 1 የአብራም ሚስት ሦራ ልጅ አልወለደችለትም ነበር፤ ነገር ግን አጋር የምትባል ግብፃዊት አገልጋይ ነበረቻት። \v 2 አብራምንም፣ "ያህዌ ልጅ እንዳልወደልድ አድርጎኛል። ምናልባት በእርሷ በኩል ልጅ አገኝ ይሆናልና ክአገልጋዬ ጋር ተኛ" አለችው። አብራም ሦራ በነገረችው ተስማማ። \v 3 የአብራም ሚስት ሦራ ግብፃዊት አገልጋይዋ ሚስት እንድትሆነው ለአብራም የሰጠችው አብራም በከነዓን ምድር አሥር ዓመት ከኖረ በኋላ ነበር። \v 4 አብራም ክአጋር ግን'ኡንት አደረገ እርሷም ፀነሰች። አጋር መፅነሷን ባወቀች ጊዜ እመቤቷን በንቀት ማየት ጀመረች።

1
16/05.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 5 በዚህ ጊዜ ሦራ አብራምን፣ "ይህ በደል የደረሰብኝ በአንተ ምክንያት ነው። ኅቅፍህ ውስጥ እንድትሆን አገልጋዬን ሰጠሁ፤ እርሷ ግን መፅነሷን ስታውቅ እኔን መናቅ ጀመረች። ያህዌ በእኔና በአንተ መካከ ይፍረድ" አለችው። \v 6 አብራምም መልሶ ሦራን፣ "አገልጋይሽ እኮ በእጅሽ ውስጥ ናት እርሷ ላይ የፈለግሽውን ማድረግ ትችያልለሽ" አላት። ስለዚህ ሦራ ስላሠቃየቻት፣ አጋር ከቤት ጠፍታ ሄደች።

1
16/07.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 7 የያህዌ መልአክ አጋርን ምድረ በዳ ውስጥ በነበረ አንድ ምንጭ አጠገብ አገኛት፤ ያ ምንጭ ወደ ሱር በሚወስደው መንገድ ላይ ነበር። \v 8 መልአኩም፣ "የሦራ አገልጋይ አጋር ሆይ፣ ከየት መጣሽ ወዴትስ እየሄድሽ ነው?" አላት። እርሷም፣ "ከእመቤቴ ከሦራ ኮብልዬ እየሄድሁ ነው" አለችው።

1
16/09.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 9 የያህዌ መልአክ፣ "ወደ እመቤትሽ ተመለዒ፤ ራስሽንም ለሥልጣንዋ አስገዢ" አላት። \v 10 ከዚያም የያህዌ መልአክ፣ "ዘርሽን እጅግ አበዛዋለሁ፤ ከበምዛቱም የተነሣ ሊቆጠር አይቻልም" አላት።

1
16/11.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 11 የያህዌም መልአክ በተጨማሪ እንዲህ አላት፤ "እነሆ ፀንሰሻል ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ያህዌ ችግርሽን ሰምቷልና ስሙን እስማኤል ትዪዋለሽ። \v 12 እርሱ እንደ ዱር አህያ ይሆናል። ከሰው ሁሉ ጋር ይጣላል፤ ሰው ሁሉም ከእርሱ ጋር ይጣላል፤ ከወንድሞቹ ሁሉ ተነጥሎ ይኖራል።"

1
16/13.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 13 እርሷም ይሚያናግራትን ያህዌን፣ "አንተኮ እኔን የምታይ አምላክ ነህ"በማለት ጠራችው፤ ምክንያቱም፥ "እርሱ እኔን እንዳየ ሁሉ እኔም እርሱን አየው ይሆን?" ብላ ነበር። \v 14 ስለዚህ ያ ምንጭ ብኤርልያህሮኢ ተባለ፤ የሚገኘው በቃዴስና በባሬድ መካከ ልነው።

1
16/15.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 15 አጋር ለአብራም ወድን ልጅ ወለደችለው፤ አብራምም አጋር የወለደችለትን ልጅ እስማኤል ብሎ ጠራው። \v 16 አጋር እስማኤልን በወለደች ጊዜ አብራም ሰማንያ ስድስት ዓመት ሆኖት ነበር።

1
16/title.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
ምዕራፍ 16

1
17/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\c 17 \v 1 አብራም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው እያለ ያህዌ ተገለጠለትና እንዲህ አለው፤ "እኔ ሁሉን ቻይ አምላክ ነኝ፤ በፊቴ ተመላለስ ነቀፋም አይኑርብህ። \v 2 በእኔና በአንተ መካከል የተደረገውን ኪዳን አጸናለሁ፤ አንተንም እጅግ አበዛሃለሁ።"

1
17/03.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 3 አብራም በግንባሩ መሬት ላይ ተደፋ፤ እግዚአበሔርም እንዲ አለው፤ \v 4 "እነሆ ኪዳኔ ክአንተ ጋር ነው። የብዙ ሕዝብ አባት አደርግሃለሁ። \v 5 ከእንግዲህ ስምህ አብራም መባል የለበትም፤ ስምህ አብርሃም መባል እለበት፤ ምክንያቱም የብዙ ሕዝብ አባት አድርጌሃለሁ። \v 6 እጅግ አበዛሃለሁ፣ ሕዝቦች ክአንተ ይገኛሉ፤ ነገሥታትም ክአንተ ይወጣሉ።

1
17/07.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 7 በእኔና በአንተ፣ ክአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር ኪዳኔን እመሠርታለሁ፤ ለአንተ ከአንተም በኋላ ለዘርህ በዘላለም ኪዳን አምላክ እሆናችኋለሁ። \v 8 ለአንተና ከአንተም በኋላ ለዘርህ ይህች አሁን የምትኖርባትን የከነዓንን ምድር በሙሉ ለዘላለም ርስት አድርጌ እሰጣላለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ።"

1
17/09.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 9 ከዚያም እግዚአብሔር አብርሃምን፣ "በአንተም በኩል፣ አንተና ከአንተ በኋላ የሚመጣው ዘርህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ኪዳኔን መጠበቅ አለባችሁ። \v 10 በእኔና በአንተ መካከል ከአንተም በኋላ በእኔና በዘርህ መካከል መጠበቅ ያለባችሁ ኪዳኔ ይህ ነው፤ በመካከላችሁ ያለ ወንድ ሁሉ ይገረዝ። \v 11 እናንተ ሸለፈታችሁን ትገረዛላችሁ፤ ይህም በእናንተ መካከል ያለው ኪዳን ምልክት ይሆናል።

1
17/12.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 12 በመካከላችሁ ያለው ማንኛውም ስምንት ዓመት የሞላው ወንድ የሚመጣው ትውልድ ሁሉ ይገረዝ። ይህ በቤትህ የተወለደውን በገንዘብህ የተገዛውን ሁሉ ይጨምራል። \v 13 ቤትህ ውስጥ የተወለደና በገንዘብህ የገዛኸው መገረዝ አለባቸው። ስለሆነም ኪዳኔ በዘላለም ኪዳን ሥጋችሁ ላይ ይሆናል። \v 14 ሸለፈቱን ያልተገረዘ ማንኛውም ወንድ ኪዳኔን አፍርሷልና ከወገኖቹ ይወገድ።"

1
17/15.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 15 እግዚአብሔር አብርሃምን እንዲህ አለው፤ "ሚስትህ ሦራን ክአንግዲህ ሥራ እንጂ ሦራ ብለህ አትጥራት። \v 16 እባርክሃለሁ፤ ከእርሷ ወንድ ልጅ እሰጥሃለሁ። እባርካታለሁ። እርሷም የብዙ ሕዝብ እናት ትሆናልች፤ የሕዝቦችም ነገሥታት ክአርሷ ይወጣሉ።

1
17/17.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 17 በዚህ ጊዜ አብርሃም በግንባሩ መሬት ላይ ተደፍቶ እየሳቀ በሉ እንዲህ አለ፤ "ለመሆኑ የመቶ ዓመት ሽማግሌ ልጅ መውልደድ ይችላል? የዘጠና ዓመቷ አሮጊት ሥራስ ብትሆን ልጅ መውለድ ይሆንላታል?" \v 18 አብርሃም እግዚአብሔርን፣ "ይልቅ፣ እስማኤልን ብቻ ባኖርህልኝ!" አለ።

1
17/19.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 19 እግዚአብሔርም፣ "እንደዚያ አይደለም፤ ሚስትህ ሥራ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ይስሐቅ ብለህ ትጠራዋለህ። የዘላለም ኪዳኔን ከእርሱ ጋር፣ ከእርሱም በኋላ ከዘሩ ጋር እመጸርታለሁ። \v 20 እስማኤልን በተመለከተም ልምናህን ሰምቻለሁ። እነሆ እርሱንም እባርከዋለሁ፤ ፍሬያማም አደርገዋለሁ፤ እጅግም አበዛዋለሁ። የአሥራ ሁለት ነገዶች አባት ይሆናል፤ ታላቅ ሕዝብ እንዲሆንም አደርጋለሁ። \v 21 ኪዳኔን ግን፣ የዛሬ ዓመት በዚህ ጊዜ ሣራ ከምትወልድህል ከይስሐቅ ጋር እመሠርታለሁ።"

1
17/22.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 22 ከእርሱ ጋር መነጋገሩን ከጨረሰ በኋላ እግዚአብሔር ወደ ላይ ወጣ። \v 23 በዚያኑ ዕለት አብርሃም ልጁ ይስሐቅን፣ በቤቱ ውስጥ የተወለዱትን በሙሉ፣ በገንዘቡ የገዛቸውን ሁሉ፣ ቤቱ ውስጥ ያለ ማንኛውንም ወንድ ሁሉ እግዚአብሔር በነገረው መሠረት ገረዛቸው።

2
17/24.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 24 አብርሃም በተገረዘ ጊዜ እድሜው ዘጠና ዘጠኝ ዓመት ነበር። \v 25 ልጁም እስማኤል በተገረዘ ጊዜ እድሜው አሥራ ሦስት ነበር።
\v 26 በዚያው ቀን አብርሃምና ልጁ እስማኤልም ተገረዙ። \v 27 ቤቱ ውስጥ የተወለዱትን፣ ከውጭ በገንዘብ የተገዙትን ጨምሮ ቤቱ ውስጥ የነበሩ ወንዶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ተገረዙ።

1
17/title.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
ምዕራፍ 17

1
18/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\c 18 \v 1 ቀኑ በጣም ሞቃት በሆነ ጊዜ አብርሃም በመምሬ ወርካ ዛፎች አቅራቢይ ኣድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ እያለ ያህዌ ተገለጥለት። \v 2 እርሱም ቀና ብሎ ሦስት ሰዎች ፊት ለፊቱ ቆመው አየ። ባያቸውም ጊዜ ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ፈጥኖ ወደ እነርሱ ሄዶ፣ ወደ መሬት ዝቅ ብሎም እጅ ነሣ።

1
18/03.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 3 አብርሃም እንዲህ አለ፤ "ጌታዬ፣ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ፣ ባሪያህን አልፈህ አትሂድ። \v 4 ጥቂት ውሃ ትምጣላችሁና እግራችሁን ታጠቡ፤ ከዚያም ዛፉ ሥር ዐረፍ በሉ። \v 5 ወደ እኔ ወዳገልጋያችሁ ከመጣችሁ የደከመ ሰውነታችሁ እንዲበረታ እስቲ ጥቂት እህል ላምጣላችሁና ብሉ፤ ከዚያ ጕዞአችሁን ትቀጥላላችሁ።" እነርሱም. "እንዳልኸው አድርግ" አሉት።

1
18/06.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 6 ያኔውኑ አብርሃም በፍጥነት ሣራ ወደ ነበረችበት ድንኳን ገብቶ፣ "ቶሎ ብለሽ ሦስት መስፈሪያ ስልቅ ዱቄት አቡኪና ቂጣ ጋግሪ" አላት። \v 7 ከዚያም ወደ መንጋው በፍጥነት ሄዶ አንድ ፍርጥም ያለ ሥጋው ግን ገር የሆነ ጥጃ መረጠና ለአገልጋዩ ሰጠው፤ እርሱም በአስቸኳይ አደረሰው። \v 8 አብርሃምም እግሮ፣ ወተትና የተዘጋጀውን የጥጃ ሥጋ አቀበላቸው፤ እነርሱ እየበሉ እያለ እርሱ ዛፉ ሥር አጠገባቸው ቆሞ ነበር።

1
18/09.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 9 እነርሱም እንዲህ አሉት፤ "ሚስትህ ሥራ የታለች?" እርሱም፣ "ድንኳን ውስጥ ናት" አለ። \v 10 እነርሱም፣ "የዛሬ ዓመት በፀደይ ወቅት ልክ በዚሁ ጊዜ በእርግጥ ተመልሼ እመጣለሁ፤ ሚስትህ ሥራ ልጅ ትወልዳለች" አለ። ሥራ ከጀርባ በነበረው ድንኳን ደጃፍ ሆና ታዳምጥ ነበር።

1
18/11.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 11 በዚህ ጊዜ አብርሃምና ሥራ በጣም አርጅተው ነበር፤ ሥራማ ልጅ የመውለጃ ጊዜ አልፎባት ነበር። \v 12 ስለዚህ ሣራ በልቧ፣ "ይህን ያህል ካረጀሁና ጌታዬም ከደከመ በኋላ በዚህ ነገር መደሰት ይሆንልኛልን?" ብላ ሳቀች።

1
18/13.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 13 ያህዌ አብርሃምን እንዲህ አለው፤ "ካረጀሁ በኋላ እንዴት አድርጌ ልጅ እወልዳለሁ ስትል ሣራ የሳቀችው ለምንድን ነው? \v 14 ለመሆኑ ለያህዌ የሚሳነው ነገር አለ? እኔ በወሰንሁት የፀደይ ወቅት ወደ እናንተ እመለሳለህ፤ በሚመጣው ዓመት በዚህ ጊዜ ሥራ ወንድ ልጅ ትወልዳለች።" \v 15 ሣራ ግን ፈርታ ስል ነበር፣ "ኧረ እልሳቅሁም" በማለት ካደች። እርሱም፣ "የለም፤ ስቀሻል እንጂ" አላት።

1
18/16.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 16 ሰዎቹ ለመሄድ ሲነሡ ቁልቁል ወደ ሰዶም ተመለከቱ። አብርሃምም ሊሸኛቸው ከእነርሱ ጋር ሄደ። \v 17 በዚህ ጊዜ ያህዌ እንዲህ አለ፤ "እኔ የማደርገውን ክአብርሃም መደበቅ አለብኝን? \v 18 አብርሃም በእርግጥ ታላቅና ብርቱ ሕዝብ ይህሆናል፤ የምድር ሕዝቦችም ሁሉ በእርሱ ይባረካሉ። \v 19 ትክክለኛና ቀና የሆነውን በማድረግ የያህዌን መንገድ እንዲጠብቁ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤተ ሰቡን እንዲያስተምር እኔ አብርሃምን መርጬዋለሁ፤ ይኸውም ለአብርሃም የነገረውን ሁሉ ያህዌ እንዲፈጽምለት ነው።"

1
18/20.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 20 ደግሞም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ "በሰዶምና በገሞራ ላይ የሚሰማው ክስ በጣም ስለ በዛ፣ ኀጢአታቸውም በጣም ትልቅ ስል ሆነ፤ \v 21 ወደ እኔ የመጡ ክሶች ምን ያህል እውነት መሆናቸውን ለማየት ወደዚያ እወርዳለሁ፤ እንደዚይ ካልሆነም አውቃለሁ።"

1
18/22.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 22 ሰዎቹም ፊታቸውን ወደ ሰዶም አቅንተው ሄዱ፤ አብርሃም ግን ያህዌ ፊት እንደ ቆመ ነበር። \v 23 አብርሃም ወደ እርሱ ቀረብ ብሎ፣ "በእርግጥ ጻድቁን ከኀጢአተኛው ጋር ታጠፋለህን?

1
18/24.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 24 ምናልባት በከተማዋ ሃምሳ ጻድቃን ቢገኙስ? እዚያ ባሉ ጻድቃን ስትል ከተማዋን ሳታድን ታጠፋታለህን? \v 25 ጻድቁን ከኀጢአተኛው ጋር በመግደል፣ ኀጢአተኛ ላይ የደረሰው በእርሱም እንዲደርስ ማድረግን የመሰለ ንገር ከአንተ ይራቅ! እንዲህ ያለው ከአንተ ይራቅ! የምድር ሁሉ ዳኛ እውነተኛ ጻድቅ የሆነውን አያደርግምን? \v 26 ያህዌም እንዲህ አለ፤ "በሰዶም ከተማ ውስጥ ሃምሳ ጻድቃን ካገኘሁ ፣ ለእነርሱ ስል ያንን ቦታ እምራለሁ።"

1
18/27.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 27 አብርሃምም መልሶ እንዲህ አለ፤ "እኔ ትቢያና ዐመድ ሆኜ ሳለሁ ከጌታዬ ጋር ለመናገር አንዴ ደፍሬአለሁ፤ \v 28 ለመሆኑ ከአምሳዎቹ ጻድቃን አምስት ቢጎድሉ፣ በጎደሉት አምስቱ ምክንያት ከተማዋን በሙሉ ታጠፋለህን?" እርሱም፣ "እዚያ አርባ አምስ ጻድቃንካገኘሁ አላጠፋትም" አለ።

1
18/29.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 29 አብርሃምም እንደ ገና፣ "ምናልባት አርባ ጻድቃን ቢገኙስ?" እለ፤ እርሱም፣ "ለአርባዎቹ ስል አላደርገውም" እለ። \v 30 አብርሃምም፣ "እባክህን ጌታዬ ይህን ያህል በመናገሬ አትቆጣኝ። እንደው ምናልባት ሰለሣ ቢገኙስ" አለ። እርሱም መልሶ፣ "ሰላሣ ጻድቃን ካገኘሁ አላደርገውም" በማለት መለሰ። \v 31 አብርሃምም፣ "መቼም አንዴ ከጌታዬ ጋር መናገር ጀምሬአለሁ! እንደው ምናልባት ሃያ ቢገኙስ" አለ። እርሱም መልሶ፥ "ለሃያዎቹ ስል አላደርገውም" አለ።

1
18/32.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 32 በመጨረሻም እንዲህ አለ፤ "እባክህ ጌታዬ አትቆጣኝ፤ አንዴ ብቻ ልናገር፤ ምናልባት አሥር ቢገኙስ። እርሱም፣ "ለአሥሩ፣ ሲል አላጠፋትም" አለ። \v 33 ከአብርሃም ጋር መነጋገሩን እንደ ጨረሰ ያህዌ ሄደ፤ አብርሃምም ወደ ቤቱ ተመለሰ።

1
18/title.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
ምዕራፍ 18

1
19/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\c 19 \v 1 ሁለቱ መላእክት ምሽት ላይ ወደ ሰዶም መጡ፤ በሰዶም ከተማ መግቢያበር ላይ ተቀምጦ ነበር። ሎጥ ሲያያቸው ሊቀበላቸው ተነሣ፤ በግንባሩም መሬት ላይ ተደፋ። \v 2 እርሱም፣ "እባካችሁ ጌቶቼ ወደ እኔ ወደ ባሪያችሁ ቤት ጎራ በሉ፤ እግራችሁን ታጠቡ፤ ሌሊቱንም ከእኛ ጋር አሳልፉ፤ ከዚያ ጧት በማለዳ ተነሥታችሁ ጕዞአችሁን ትቀጥላላችሁ።" እነርሱም፣ "የለም፤ እዚሁ አደባባዩ ላይ እናድራለን" አሉት። \v 3 ሎጥ ግን አጥብቆ ስለ ለመናቸው እርሱ ቤት ለማደር አብረውት ገቡ። ከዚያም ቂጣ ጋግሮ አቀረበላቸው፤ እነርሱም በሉ።

1
19/04.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 4 ሆኖም፣ ገና ከመተኛታቸው በፊት የሰዶም ከተማ ነዋሪዎች የሆኑ ወጣቶችና ሽማግሌዎች ከየአካባቢው መጥተው ቤቱን ከበቡት። \v 5 ሎጥን በመጣራት፣ "በዚህ ምሽት ወደ ቤትህ የመጡ ሰዎች የታሉ? ሩካቤ ሥጋ እንድንፈጽምባቸው ወደ ውጭ አውጣልን" አሉት።

1
19/06.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 6 ሎጥ ሊያነጋግራቸው ወደ ውጭ ወጣ መዝጊያውን ከበስተ ኋላው ዘጋ። \v 7 እንዲህም አለ፤ "ወንድሞቼ እንዲህ ያለ ክፉ ነገር እንዳታደርጉ እለምናችሏለሁ። \v 8 ከወንድ ጋር ተኝተው የማያውቁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ፤ እነርሱን ላውጣላችሁና የወደዳችሁትን አድርጉባቸው። በእነዚህ ሰዎች ላይ ግን ምንም ነገር አታድርጉባቸው፤ እኔን ብለው ወደ ቤቴ ተብተዋልና።"

1
19/09.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
እነርሱ ግን፣ "ዞር በል!" ይኸ ሰውዬ ስደተኛ ሆኖ እዚህ ለመኖር መጣ፤ ደግሞ ዳኛ ሆነብን! ይልቁ በእነርሱ ላይ ካሰብነው የከፋ እንዳይደርስብህ ዘወር በልልን" አሉት ሎጥንም እየገፈታተሩ የበሩን መዝጊያ ለመስበር ተቃርበው ነበር።

1
19/10.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 10 ሰዎቹ እጃቸውን ዘርግተው ሎጥን ወደ ቤት አስገቡትና በሩን ዘጉ። \v 11 ከቤቱ ውጪ የነበሩትን ውጣቶችንም ሆን ሽማግሌዎችን ግን የሎጥ እንግዶች ዐይናቸውን አሳወሩአቸው፤ እነርሱም በሩን ለማግኘት ይደነባበሩ ጀመር።

1
19/12.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 12 ከዚያም ሰዎቹ ሎጥን እንዲህ አሉት፤ "በከተማዋ የሚኖሩ የአንተ የሆኑ ሰዎች አሉህ? ወንዶችና ሴቶች ልጆችህን፣ የወንዶች ልጆችህን ሚስቶች፣ የሴቶች ልጆችህን ባሎችና ሌሎች ዘመዶችህን ሁሉ ከዚህ አውጣ። \v 13 ምክንያቱም ይህን ቦታ ልናጠፋ ነው፤ በያህዌ ፊት ከተማዋ ላይ የሚቀርቡ ክሶች በጣም እየጮኹ በመሆናቸው እንድናጠፋት እርሱ ልኮናል።"

1
19/14.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 14 ሎጥ ከቤቱ ወጥቶ የሴት ልጆቹን ባሎች፣ የሴት ልጆቹን እጮኞች፣ "ቶሎ ከዚህ ቦታ ውጡ፤ ያህዌ ከተማዋን ሊያጠፋ ነው" አላቸው። የሴት ልጆቹ ባሎች ግን የሚቀልድ መሰላቸው። \v 15 ሲነጋጋም መላእክቱ ሎጥኝ፣ "ከተተማዋ ላይ በሚመጣው ቅጣት አብራችሁ እንዳትጠፉ ሚስትህንና ሁለቱ ሴት ልጆችህን ይዘህ ከዚህ ቦታ በፍጥነት ውጣ" እያሉ አቻኮሉት።

1
19/16.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 16 ሎጥ አመነታ፤ ያህዌ ምሕረት ስላደረገላቸው ሰዎቹ የእርሱ፣ የሚስቱንና የሁለት ሴት ልጆቹን እጅ ይዘው ከከተማዋ አወጣቸው። \v 17 ከከተማው ካወጧቸው በኋላ ከሰዎቹ አንዱ፣ "ሕይወታችሁን ለማዳን ሩጡ! ወደ ኋላችሁ አትመልከቱ፤ ወይም ረባዳው ስፍራ ላይ አትቆዩ። ወደ ተራሮች ሽሹ፤ አለበለዚያ ትጠፋላችሁ።"

1
19/18.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 18 ሎጥም እንዲህ አላቸው፤ "ጌቶቼ ሆይ፣ \v 19 እኔ ባሪያችሁ በፊታችሁ ሞገስ አግኝቻለሁ፤ ሕይወቴን ለማዳን ታላቅ ርኅራኄ አድርጋችሁልኛል፤ እኔ እንደ ሆንኩ ወደ ተራሮቹ ሸሽቼ ማምለጥ ስለማልችል የሚወርደው መዓት ደርሶ ያጠፋኛል። \v 20 ወደዚያ ሸሽቶ ለማምለጥ ቅርብ ቦታ ያለች ትንሽ ከተማ አለች ሸሽቼ ወደዚያ ብሄድ ሕይወቴን ማዳን እችላለሁ።"

1
19/21.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 21 እርሱም፣ "ይሁን እሺ፤ ልመናህን ተቀብብያለሁ፤ ያክካትንም ከተማ አላጠፋትም። \v 22 አንተ እዚያ እስክትደርስ ምንም ማድረግ ስለማልችል በል ቶሎ ፍጠንና ወደዚያ ሽሽ" አለው። ስለዚህ ያቺ ከተማ ዞዓር ተባለች።

1
19/23.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 23 ሎጥ ዞዓር ሲደርስ ፀሓይ በምድሩ ወጥታ ነበር። \v 24 ከዚያ ያህዌ ሰዶምና ጎሞራ ላይ ድኝና እሳት አዘነበ። \v 25 እነዚያን ከተሞችና ረባዳ ቦታዎቹን፣ የከተሞቹ ነዋሪዎችንና እዚይ ኣያሉ ለምለም ነገሮችን ሁሉ አጠፋ።

1
19/26.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 26 ከኋላው የነበረችው የሎጥሚስት ግን ወደ ኋላዋ ስለ ተመለከተች የጨው ዐምድ ሆና ቀረች። \v 27 አብርሃም ጠዋት ማለዳ ተነሥቶ ያህዌ ፊት ቆሞ ወደ ነበረበት ቦታ ሄደ። \v 28 ቁልቁል ሰዶምና ጎሞራን፣ እንዲሁም በረባዳው ስፍራ የነበረውን ምድር ተመለከተ። ከምድጃ የሚወጣ የመሰለ ጢስ ከምድሩ እየወጣ ነበር።

1
19/29.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
እግዚአብሔር በረባዳው ቦታ የነበሩ ከተሞችን ባጠፋ ጊዜ አብርሃምን አሰበው። ሎጥ የነበረበትን ከተሞች ቢያጠፋም፣ እርሱ ግን ከጥፋት መሐል አወጣው።

1
19/30.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 30 ሎጥ ግን በዞዓር መኖር ስለ ፈራ ከሁለት ሴቶች ልጆቹ ጋር ተራሮቹ ላይ ለመኖር ከዞዓር ወደ ላይ ወጣ። ስለዚህ እርሱና ሁለት ሴቶች ልጆቹ ዋሻ ውስጥኖሩ።

1
19/31.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 31 ታላቋ ልጅ ታናሿን እንዲህ አለቻት፣ "አባታችን አርጅቷል፤ በምድር ሁሉ እንደሚኖሩ ሰዎች ወግ ከእኛ ጋር የሚተኛ ወንድ በአካባቢያችን የለም። \v 32 ስለዚህ አባታችንን የወይን ጠጅ እናጠጣውና ከእርሱ ጋር እንተኛ፤ የትውልድ ሐረጋችን እንዳይቋረጥ ከአባታችን ዘር እናትርፍ።" \v 33 ስለዚህ በዚያ ምሽት አባታቸውን የወይን ጠጅ አጠጡት። ታላቂቱ ልጅ ሄዳ ክአባቷ ጋር ተኛች፤ እርሷ ስትተኛም ሆነ ስትነሣ አላወቅም።

1
19/34.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 34 በሚቀጥለው ቀን ታላቂቱ ታናሺቱን እንዲህ አለቻት፤ "ትናንት ሌሊት እኔ ከእባቴ ጋር ተኛሁ። ዛሬም እንደ ገና የወይን ጠጅ እናጠጣው፣ ከዚያ አንቺ ሄደሽ ከእርሱ ጋር ትተኛለሽ፣ የአባታችንንም ዘር እናተርፋለን።" \v 35 ስለዚህ በዚያም ምሽት አባታቸውን ወይን ጠጅ አጠጡት፤ ታናሺቱ ልጅ ሄዳ ከእርሱ ጋር ተኛች፤ እርሷ ስትተኛም ሆነ ስትነሣ አላወቀም።

1
19/36.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 36 ሁለቱ የሎጥ ልጆች ክአባታቸው አረገዙ። \v 37 ታላቂቱ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሞዓብ አለችው። እርሱም ዛሬ ያሉት ሞዓባውያን አባት ሆነ። \v 38 ታናሺቱም እንዲሁ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ቤንአሚ አለችው። እርሱም ዛሬ ያሉት አሞናውያን አባት ሆነ።

Some files were not shown because too many files have changed in this diff Show More