\c 5 \v 1 ክርስቶስ ነጻ ያወጣን በነጻነት እንድንኖር ነው ። ስለዚህ ጸንታችሁ ቁሙ፥ እንደገና በባርነት ቀንበር አትጠመዱ። \v 2 እኔ ጳውሎስ የምለውን ተመልከቱ ብትገረዙ ክርስቶስ በምንም ዓይነት መልኩ አይጠቅማችሁም።