am_gal_text_ulb/02/01.txt

1 line
622 B
Plaintext

\c 2 \v 1 ከአስራ አራት ዓመት በኋላ ቲቶን ይዤ ከበርናባስ ጋር እንደገና ወደ ኢየሩሳሌም ሄድኩ። \v 2 የሄድኩበትም ምክንያት መሄድ እንዳለብኝ እግዚአብሔር ስላመለከተኝ ነበር። ሄጄም በአህዛብ መካከል እየሰበኩት ስላለው ወንጌል ነገርኳቸው፣ ነገር ግን በከንቱ እንዳልሮጥኩ ወይም እየሮጥኩ እንዳልሆን እርግጠኛ ለመሆን ይህን የተናገርኩት በሌሎቹ ዘንድ እንደ ዋና ለሚታሰቡት ብቻ ነበር።