am_ezr_text_udb/10/01.txt

1 line
750 B
Plaintext

\c 10 \v 1 በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ተንበርክኮ ሲጸልይና ሲያለቅስስ እስራኤላዊያን የሰሩትን ኃጢአቶች ይናዘዝ ነበር፡፡ ብዙ ሰዎች፣ ወንዶችና ሴቶች እንዲሁም ልጆች በዙሪያው ተሰብስበው እጅግ ያለቅሱ ነበር፡፡ \v 2 ከዚያ ከኤላም ጎሣ የይሒኤል ልጅ ሴኬንያ፣ ዕዝራን እንዲህ አለው፡ “እኛ እግዚአብሔርን ሳንታዘዝ ቀርተናል አንዳንዶቻችን እስራኤላዊ ያልሆኑ ሴቶችን አግብተናል፡፡ ነገር ግን አሁንም ቢሆን ያህዌ እስራኤልን እንደሚምር ተስፋ ልናደርግ እንችላለን፡፡