am_ezr_text_udb/03/10.txt

3 lines
977 B
Plaintext

\v 10 ግንበኞቹ የቤተመቅደሱን መሠረት ጥለው ሲጨርሱ፣ ካህናቱ የክህነት ልብሶቻቸውን ለብሰው መለከቶችን እየነፉ በየስፍራቸው ቆሙ፡፡ ከዚያ የአሳፍ ትውልድ የሆኑት ሌዋውያን ጸናጽላቸውን እየወዘወዙ ያህዌን አወደሱ፣ ይህም ልክ ንጉስ ዳዊት ከብዙ አመታት በፊት ለአሳፍና ለሌሎች ዘማሪያን እንደተናገረው ተደረገ፡፡ \v 11 ያህዌን አወደሱ፣ አመሰገኑትም፣ ስለ እርሱም ይህን መዝሙር ዘመሩ፡
“እርሱ ለእኛ እጅግ መልካም ነው! ለእስራኤል ቃል ኪዳኑን በታማኝነት አክብሯል ደግሞም ለዘለዓለም ይወደናል፡፡”
ከዚያ ህዝቡ ሁሉ የቤተመቅደሱ መሠረት ስላለቀ እግዚአብሔርን አወደሱት፡፡ በእልልታም አመሰገኑት፡፡