am_ezk_text_ulb/09/03.txt

1 line
530 B
Plaintext

\v 3 የእስራኤልም አምላክ ክብር በበላዩ ከነበረበት ከኪሩብ ላይ ተነሥቶ ወደ ቤቱ መድረክ ሄደ። በፍታም የለበሰውን የጸሐፊውንም ቀለም ቀንድ በወገቡ የያዘውን ሰው ጠራ። \v 4 እግዚአብሔርም "በኢየሩሳሌም ከተማ መካከል እለፍ፥ በመካከልዋም ስለ ተሠራው ርኵሰት ሁሉ በሚያለቅሱና በሚተክዙ ሰዎች ግምባር ላይ ምልክት አድርግ" አለው።