am_ezk_text_ulb/48/23.txt

1 line
749 B
Plaintext

\v 23 ለቀሩትም ነገዶች ድርሻቸው ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ይሆናል። የብንያም ነገድ አንድ የዕጣ ክፍል ይቀበላል። \v 24 ከብንያምም ደቡባዊ ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለስምዖን አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል። \v 25 ከስምዖንም ደቡባዊ ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለይሳኮር አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል። \v 26 ከይሳኮርም ደቡባዊ ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለዛብሎን አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል።