am_ezk_text_ulb/48/21.txt

1 line
821 B
Plaintext

\v 21 በተቀደሰው መባና በከተማይቱ ይዞታ በዚህና በዚያ ወገን የቀረው ሥፍራ ለአለቃው ይሆናል። በምስራቅ በኩል ያለው የአለቃው ኩታ ገጠም መሬት ከተቀደሰው የመሬት መባ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ወደ ምሥራቁ ድንበር፥ በምዕራብም በኩል ደግሞ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ወደ ምዕራቡ ድንበር ይዘልቃል። የተቀደሰውም የመሬት መባውና የቤተ መቅደሱ የተቀደሰ ስፍራ በመካከል ይሆናል። \v 22 የአለቃውም ይዞታው ከሌዋውያን ርስትና ክከተማይቱ ይዞታ መካከል ይሆናል፤ በይሁዳ ድንበርና በብንያም ድንበርም መካከል ይሆናል።