am_ezk_text_ulb/47/18.txt

1 line
660 B
Plaintext

\v 18 የምሥራቁም ድንበር በሐውራን በደማስቆና በገለዓድ በእስራኤልም ምድር መካከል ዮርዳኖስ ይሆናል። ይህም ድንበር እስከ ታማር ድረስ ይሄዳል። \v 19 የደቡቡም ድንበር ከደቡብ ታማር ጀምሮ እስከ ሜርባ ቃዴስ ውኃ እስከ ግብጽ ወንዝ እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ይሆናል። የደቡቡ ድንበር ይህ ነው። \v 20 የምዕራቡም ድንበር ከታላቁ ባሕር ጀምሮ እስከ ሐማት መግቢያ አንጻር ድረስ ይሆናል። የምዕራቡ ድንበር ይህ ነው።