am_ezk_text_ulb/47/01.txt

1 line
626 B
Plaintext

\c 47 \v 1 ወደ መቅደሱም መዝጊያ መለሰኝ እነሆም፥ ውኃ ከቤቱ መድረክ በታች ወደ ምሥራቅ ይወጣ ነበር፥ የቤቱ ፊት ወደ ምሥራቅ ይመለከት ነበርና ውኃውም ከመስዊውው በስተቀኝ በኩል ወደ ቤተመቅደሱ ደቡብ አቅጣጫ ይወርድ ነበር። \v 2 በሰሜኑም በር በኩል አወጣኝ በስተ ውጭ ባለው መንገድ፥ ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከት በስተ ውጭ ወዳለው በር መራኝ እነሆም፥ ውኃው ከበሩ ምዕራብ ወገን ይፈስስ ነበር።