am_ezk_text_ulb/46/21.txt

1 line
822 B
Plaintext

\v 21 በውጭው አደባባይ አወጣኝ በአደባባይም ወዳለው በአራቱ ማዕዘን በኩል አሳለፈኝ እነሆም፥ በእያንዳንዱ የአደባባዩ ማዕዘን ሌላ አደባባይ እንዳለ አየሁ። \v 22 በአደባባዩ በአራቱ ማዕዘን ርዝመቱ አርባ ክንድ ወርዱም ሠላሳ ክንድ የሆነ አደባባይ ነበረ። በማዕዘኑ ላሉ ለእነዚህ ለአራቱ ስፍራዎች አንድ ልኬቱ እኩል ነበረ። \v 23 በአራቱም ዙሪያ ሁሉ ግንብ ነበረ፥ በግንቡም ሥር በዙሪያው የመቀቀያ ቦታ ነበረ። \v 24 ሰውዬውም፥ "እነዚህ የቤቱ አገልጋዮች የሕዝቡን መሥዋዕት የሚቀቅሉባቸው ስፍራዎች ናቸው አለኝ።