am_ezk_text_ulb/46/01.txt

1 line
717 B
Plaintext

\c 46 \v 1 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በውስጠኛው አደባባይ ወደ ምሥራቅ የሚመለከተው በር ሥራ በሚሠራበት በስድስቱ ቀን ተዘግቶ ይቈይ ነገር ግን በሰንበት ቀንና በመባቻ ቀን ይከፈት። \v 2 አለቃውም በስተ ውጭ ባለው በር በደጀ ሰላሙ መንገድ ገብቶ ካህናቱም የእርሱን የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት እስኪያቀርርቡ ድረስ በበሩ መቃን አጠገብ ይቁም። ከዚያም በበሩ መድረክ ላይ ሰግዶ ይውጣ ፥ በሩ ግን እስከ ማታ ድረስ አይዘጋ።