am_ezk_text_ulb/45/06.txt

1 line
689 B
Plaintext

\v 6 ለከተማ የሚሆን ሥፍራም ከተቀደሰው የዕጣ ክፍል አጠገብ ወርዱ አምስት ሺህ ርዝመቱም ሀያ አምስት ሺህ የሆነውን ስፍራ ትለያላችሁ። ይህም ከተማ ለእስራኤል ቤት ሁሉ ይሆናል። \v 7 ለአለቃ ይዞታ የሆነው የዕጣ ክፍል በተቀደሰው መባና በከተማይቱ ይዞታ አጠገብ በዚህና በዚያ ይሆናል። በምዕራብና በምሥራቅ ይሆናል። ርዝመቱም እንደ አንድ ነገድ ዕጣ ክፍል ሆኖ ከምድሩ ከምዕራቡ ዳርቻ ጀምሮ እስከ ምሥራቁ ዳርቻ ድረስ ይሆናል።