am_ezk_text_ulb/45/03.txt

1 line
817 B
Plaintext

\v 3 ከዚያ ቦታ ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ወርዱም አሥር ሺህ ክንድ የሆነ ስፍራ ትለካለህ፤ እርሱም ቅዱስ ስፍራና ቅድስተ ቅዱሳን ይሆንልሀል። \v 4 ከምድሪቱም እግዚአብሔርን ለሚያገለግሉና ሊያገለግሉትም ወደ እግዚአብሔር ለሚቀርቡት ለካህናት የተለየ ክፍል ይሆናል። ለቤቶቻቸውም የሚሆን ስፍራ ለመቅደስም የሚሆን የተቀደሰ ስፍራ ይሆናል። \v 5 ርዝመቱም ሀያ አምስት ሺህ ወርዱም አሥር ሺህ የሆነ ስፍራ ለቤቱ አገልጋዮች ለሌዋውያን ይሆናል፥ ለሚቀመጡባቸውም ከተሞች ለራሳቸውም የርስት ይዞታ ይሆናል።