am_ezk_text_ulb/45/01.txt

1 line
650 B
Plaintext

\c 45 \v 1 ርስትም አድርጋችሁ ምድሪቱን በዕጣ በምታካፍሉበት ጊዜ ለእግዚአብሔር መባ ታቀርባላችሁ። ይህም መባ የምድሪቱ የተቀደሰ ሥፍራ ሲሆን ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ወርዱም ሀያ ሺህ ክንድ ይሆናል በዳርቻው ሁሉ ዙሪያውን የተቀደሰ ይሆናል። \v 2 ከእርሱም ርዝመቱ አምስት መቶ ወርዱም አምስት መቶ ክንድ አራት ማዕዘን የሆነ ቦታ ለመቅደሱ ይሆናል በዙሪያውም ባዶ ስፍራ የሚሆን አምሳ ክንድ ይሆናል።