\v 30 ከበኵራቱ ሁሉ የተሻለው ከየዓይነቱ ከቍርባናችሁም ሁሉ የማንሣት ቍርባን ሁሉ ለካህናት ይሆናል፥ በቤታችሁም ውስጥ በረከት ያድር ዘንድ የዱቄታችሁን በኵራት ለካህናቱ ትሰጣላችሁ። \v 31 ካህናቱ የሞተ ወይም በአውሬ የተሰበረ ፥ ወፍ ወይም እንስሳ ቢሆን፥ አይበሉም።