am_ezk_text_ulb/44/20.txt

1 line
470 B
Plaintext

\v 20 ራሳቸውንም አይላጩ የራሳቸውንም ጠጕር ይከርከሙ እንጂ ጠጕራቸውን አያሳድጉ። \v 21 ካህናቱም ሁሉ በውስጠኛው አደባባይ ሲገቡ የወይን ጠጅ አይጠጡ። \v 22 መበለቲቱንና የተፈታችይቱን አያግቡ ነገር ግን ከእስራኤል ቤት ዘር ድንግሊቱን ወይም የካህን ሚስት የነበረችይቱን መበለት ብቻ ያግቡ።