am_ezk_text_ulb/44/10.txt

1 line
799 B
Plaintext

\v 10 ከእኔ ዘንድ የራቁ፥ እስራኤልም በሳቱ ጊዜ ጣዖታቸውን ተከትለው ከእኔ ዘንድ የሳቱ ሌዋውያን ኃጢአታቸውን ይሸከማሉ። \v 11 እነርሱ የመቅደሴ በሮች ጠባቂዎች በመቅደሴም ውስጥ አገልጋዮች ናቸው። ለሕዝቡም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ሌላ መሥዋዕቱን ያርዳሉ፥ ያገለግሉአቸውም ዘንድ በፊታቸው ይቆማሉ። \v 12 ነገር ግን በጣዖቶቻቸውም ፊት መስዋዕት በማቅረባቸው ለእስራኤልም ቤት የኃጢአት ዕንቅፋት ሆነዋል። ስለዚህ ኃጢአታቸውን ይሸከማሉ ብዬ እጄን አንስቼ ምያለሁ ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር!