am_ezk_text_ulb/44/06.txt

1 line
623 B
Plaintext

\v 6 ለዓመፀኛው ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፥ "ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦እናንተ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ \v 7 እንጀራዬን፥ ስብንና ደምን፥ በምታቀርቡበት ጊዜ በመቅደሴ ውስጥ ይሆኑ ዘንድ ቤቴንም ያረክሱ ዘንድ በልባቸውና በሥጋቸው ያልተገረዙትን እንግዶችን ሰዎች አግብታችኋልና፥ እነርሱም በርኵሰታችሁ ሁሉ ላይ ይጨመሩ ዘንድ ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋልና ርኵሰታችሁ ሁሉ ይብቃችሁ።