am_ezk_text_ulb/44/04.txt

1 line
625 B
Plaintext

\v 4 ቀጥሎም ከቤቱ ፊት ለፊት በሰሜኑ በር በኩል አመጣኝ። እኔም አየሁ፥ እነሆም፥ የእግዚአብሔር ክብር የእግዚአብሔርን ቤት ሞልቶት ነበር፥ እኔም በግምባሬ ተደፋሁ። \v 5 እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ " የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ እግዚአብሔርም ቤት ሥርዓትና ሕግ ሁሉ የምናገርህን ሁሉ ልብ አድርግ ሁሉ በዓይንህም ተመልከት በጆሮህም ስማ። የቤቱንም መግቢያ የመቅደሱንም መውጫ ሁሉ ልብ በል።