am_ezk_text_ulb/43/25.txt

1 line
774 B
Plaintext

\v 25 ለሰባት ቀንም በየዕለቱ ለኃጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን አውራ ፍየልን ታቀርባለህ፥ ካህናቱም ነውርም የሌለባቸውን አንድ ወይፈን ከመንጋውም የወጣውን አንድ አውራ በግ ያቀርባሉ። \v 26 ሰባት ቀን ለመሠዊያው ያስተሰርያሉ ያነጹትማል፥ እንዲሁም ይቀድሱታል። \v 27 እነዚህ ቀኖችንም መፈጸም አለባቸው፥ በስምንተኛውም ቀን ከዚያም በኋላ ካህናቱ የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን የደኅንነትንም መሥዋዕታችሁን በመሠዊያው ላይ ያደርጋሉ እኔም እቀበላችኋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦