\v 20 ከደሙም ትወስዳለህ፥ በአራቱ ቀንዶቹም በእርከኑም በአራቱ ማዕዘን ላይ በዙሪያውም ባለው ክፈፍ ላይ ትረጨዋለህ እንዲሁ ታነጻዋለህ ታስተሰርይለትማለህ። \v 21 ለኃጢአትም መሥዋዕት የሚሆነውን ወይፈን ትወስዳለህ፥ በመቅደሱም ውጭ በተዘጋጀለት ስፍራ ታቃጥለዋለህ።