am_ezk_text_ulb/43/06.txt

1 line
955 B
Plaintext

\v 6 ሰውዬው በአጠገቤ ቆሞ ሳለ ከመቅደሱ ውስጥ የሚናገረኝን ሌላ ሰው ሰማሁ። \v 7 እንዲህም አለኝ፥ "የሰው ልጅ ሆይ፥ ይህ በእስራኤል ልጆች መካከል ለዘላለም የምቀመጥበት የዙፋኔ ስፍራና የእግሬ ጫማ መረገጫ ነው፤ ዳግመኛም የእስራኤል ቤትና ነገሥታቶቻቸው በግልሙትናቸውና በጣዖት ማምለኪያ ቦታዎቻቸው ባለው በነገሥታቶቻቸው ሬሳ ቅዱስ ስሜን አያረክሱም፡፡ \v 8 ከእንግዲህ ግንብ ብቻ በመካከል በማድርግ የጣዖቶቻቸውን መድረክ በመድረኬ አጠገብ፥ የጣዖቶቻቸውን መቃኖች በመቃኔ አጠገብ በማስቀመጥ ቅዱስ ስሜን አያረክሱም። በሠሩትም ርኵሰት ቅዱስ ስሜን አረከሱ ስለዚህ በቍጣዬ አጠፋኋቸው።