am_ezk_text_ulb/42/13.txt

1 line
889 B
Plaintext

\v 13 ከዚያም እንዲህም አለኝ፥ "በውጭኛው አደባባይ ፊት ለፊት የሚገኙት የሰሜንና የደቡብ ክፍሎች ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡ ካህናት ከሁሉ ይልቅ የተቀደሰውን ምግብ የሚበሉባቸው የተቀደሱ ክፍሎች ናቸው። ስፍራው ቅዱስ ስለሆን በዚያ የተቀደሰውን ነገር የእህሉን ቍርባን የኃጢአቱንና የበደሉን መሥዋዕት ያስቀምጣሉ። \v 14 ካህናቱም አንድ ጊዜ ወደዚያ ከገቡ ሲያገለግሉ የሚለብሷቸው ልብሶች ቅዱስ በመሆናቸው ሳያወልቁ ከተቀደሰው ሥፍራ ወደውጭኛው አደባባይ መውጣት የለባቸውም። ስለዚህም ወደ ሕዝቡ ከመጠጋታቸው በፊት ሌላ ልብስ መልበስ አለባቸው።