am_ezk_text_ulb/42/10.txt

1 line
852 B
Plaintext

\v 10 በምስራቅ በኩል የውጭውን አደባባይ ተከትሎ ከቤተመቅደሱ ውስጠኛ አደባባይ ፊት ለፊት ክፍሎች ነበሩ። \v 11 በስተ ፊታቸውም የነበረ መንገድ በርዝመቱና በወርዱ በሰሜን በኩል ከነበሩት ክፍሎች ጋር ተመሳሳይ ሲሆን መግቢያዎቻቸውም በቁጥር እኩል ነበሩ። \v 12 በደቡብም በኩል ልክ በሰሜን በኩል እንዳለው ወደ ክፍሎቹ የሚያስገቡ መግቢያዎች አሉ። በውስጥ በኩል ያለው መተላለፊያ ከበላዩ መግቢያ ያለው ሲሆን መተላለፊያው ወደተለያዩ ክፍሎች ያመሩ ነበር። በምስራቅ በኩል ወደ መተላለፊያው አንደኛው ጫፍ የሚያመራ መግቢያ ነበር።