am_ezk_text_ulb/40/35.txt

1 line
724 B
Plaintext

\v 35 በሰሜንም ወዳለው በር አመጣኝ፥ በሩንም ለካው፤ ልኬቱም ከሌሎቹ በሮች እኩል ነበር። \v 36 የዘበኛ ጓዳዎቹንና የግንቡን አዕማድ መተላለፊያዎቹ ልኬታቸው ከሌሎቹ በሮች እኩል ነበር በዙሪያውም መስኮቶች ነበሩ። ርዝመቱም አምሳ ክንድ ወርዱም ሀያ አምስት ክንድ ነበረ። \v 37 መተላለፊያውም ወደ ውጭው አደባባይ ይመለከቱ ነበር በግንቡም አዕማድ ላይ በዚህና በዚያ ወገን የዘንባባ ዛፍ ተቀርጾ ነበር ወደ እርሱም የሚያደርሱ ስምንት ደረጃዎች ነበሩት።