am_ezk_text_ulb/40/32.txt

1 line
813 B
Plaintext

\v 32 ቀጥሎም ከሌሎቹ መግቢያዎች እኩል ልኬት ባለው በምስራቁ በር በኩል ወደ ውስጠኛው አደባባይ አገባኝ። \v 33 የዘበኛ ጓዳዎቹንና የግንቡን አዕማድ መተላለፊያዎቹ ሌኬታቸው ከሌሎቹ መግቢያዎች እኩል ነበር በዙሪያም መስኮቶች ነበሩ። መግቢያውና መተላልፊያው ርዝመቱም አምሳ ክንድ ወርዱም ሀያ አምስት ክንድ ነበረ። \v 34 መተላለፊያዎቹም በስተ ውጭ ወዳለው አደባባይ ይመለከቱ ነበር በግንቡም አዕማድ ላይ በዚህና በዚያ ወገን የዘንባባ ዛፍ ተቀርጾ ነበር ወደ እርሱም የሚያደርሱ ስምንት ደረጃዎች ነበሩት።